ኢህአዴግ በሚያካሂደው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ህዝቡ ቅሬታዎችን እያሰማ ነው

ጥቅምት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየስብሰባዎቹ የተሳተፉ ምንጮች ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት በየመድረኩ የጋዜጠኞች መታሰር፣ የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት አለመከበር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መባባስ፣የሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋት፣ የህወሃት የበላይነት መኖር፣ የድህነት መንሰራፋትና የዋጋ ግሽበት አለመቀረፍ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ወከባና እስር መጠናከር በተደጋሚሚ የሚነሱና ኢህአዴግ በቂ ምላሽ ሊሰጥባቸው ያልቻለባቸው አበይት ጉዳዮች መሆናቸው ታውቆአል፡፡
ጥያቄዎቹ በተለይ በግንባሩ አባላትና በካድሬዎች ጭምር የሚነሱ መሆናቸው ግንባሩን ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደጣለው የጠቀሱት ምንጮቻችን የበላይ አመራሩ በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የወሰደው አቋም የለም፡፡
በተለይ ሰሞኑን በዋቢሸበሌ ሆቴል እና በፌዴራል ፖሊስ እየተካሄደ ባለው የመንግስት መገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ስብሰባ ላይ የመንግስት ጋዜጠኞች እያነሱት ያሉት ጥያቄዎች ትምህርት ለመስጠት ከተመደቡ የኢህአዴግ ሰዎች አቅም በላይ መሆኑ ትዝብት ላይ ከመጣሉም በላይ ጠንካራ ጥያቄዎቹ እንዳስደነገጣቸው ታውቋል፡፡
በተለይ የፕሬስ ነጻነትና የጋዜጠኞች የጅምላ እስርና ስደት ጉዳይ የተነሱ ጥያቄዎች ተድበስብሰው መታለፋቸው በርካታ ጋዜጠኞችን አሳዝኖአል፡፡ አንዳንዶቹም መግባባትና መተማመን ለማይገኝበት ስብሰባ ለምን የህዝብ ሐብትና ገንዘብ እንደሚባክን በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s