ከቦሌ ለሚ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታስረው ለስቃይ እየተዳረጉ ነው

ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦሌ ለሚ በሚባለው አካባቢ የማሪያም ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መደረጉን የተቃወሙ ነዋሪዎች ከፖሊሶች በደረሰባቸው ጥቃት በርካታ ሰዎች የተጎዱ ቢሆንም፣ ፖሊስ ሃይሉን አሰባስቦ በመምጣት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይዞ አስሯል።
አብዛኞቹ ወጣቶች በኮብል ስቶን ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ ፖሊስ ወደ ድርጅቶቹ በመሄድ ወጣቶችን በጅምላ ማሰሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወንድሞቹ የታሰሩት አንድ ነዋሪ ለኢሳት ሲናገር በቦሌ ፖሊስ ጣቢያ ብቻ ከ1 ሺ ያላነሱ ወጣቶች ታስረው ውሃና ምግብ እንዳያገኙ ተከልክለው ሌሊቱን በብርድ አሳልፈዋል።
ጧት ውሃ ለማድረስ በሄደበት ጊዜ እጅግ የሚያሳዝን ትእይንት መመልከቱንም ነዋሪው ተናግሯል። ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ ወጣቶቹ በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች በመታሰራቸው ቁጥሩን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ይላሉ።
በ7 መኪኖች ተጭነው ወደ አካባቢው የደረሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ ብዙዎች እግራቸው አካባቢ ጉዳት እንደደረሰባቸው ኢሳት በትናንት ዘገባው አሰምቷል።
የማሪያም ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እድትፈርስ የተደረገ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑዋ እቃዎች በመኪና ተጭኖ ተወስዷል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s