በአማራ ክልል ባለፉት 5 አመታት ከ6ሺ በላይ ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን አጡ

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 ዓ.ም ወዲህ በተከሰተ አደጋ በክልሉ 18ሺ 994 የመኪና አደጋዎች ተከሰተዋል፡፡ በትራፊክ ሳምንት ውይይት ላይ እንደተገለፀው በአጠቃላይ በአምስት አመታት በተከሰተው አደጋ 6ሺ 668 ሰዎች ህይዋታቸውን አጠዋል፡፡
6ሺህ 581 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ፤ 11 ሺ 781 ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 994 ሚልዮን 626 ሺህ 866 ብርየሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡
በ2007 ዓ.ም 6 ወራትም 2 ሺህ 362 የትራፊክ አደጋዎች የደረሱ ሲሆን 585 ሰዎች የሞት ፤792 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ፤ 1ሺህ 436 ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። 56 ሚልዩን 432 ሺህ 523 ብር የሚገመት ንብረትም ወድሟል፡፡
እንደ ዋና ኢንስፔክተር ሙሉጌታ በዜ ገለፃ ከአመት አመት ችግሩ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። 79 በመቶ በላይ የሚሆነው አደጋ የሚከሰተው በአሸከርካሪዎች እና በእግረኛ ስህተት ሲሆን ትርፍ መጫን ፤ በሌሊት ያለ እረፍት ማሽከርከር ፤ ከመንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣን በገንዘብ ህገወጥ መንጃ ፈቃድ በመግዛት እንዲሁም በሃሰት መንጃ ፈቃድ ( ፎርጅድ) በመጠቀም ማሽከርከርም ሌሎች የአደጋ መንስኤዎች ተብለዋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s