ቦርድ የወጡ አንዳንድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሶማሊያ እንዲዘምቱ ጥሪ ቀረበላቸው

ኀዳር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም ሶማሊያ ውስጥ ዘምተው የነበሩና መከላከያን የአገልግሎት ዘመናቸውን በመጨረስ ወይም በጉዳት የለቀቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ መከላከያ ተመልሰው እንዲዘምቱ በደብዳቤ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ጥሪው የደረሳቸው ወታደሮች ጥሪውን ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም።
ጥሪ የተደረገላቸው የሰራዊት አባላት “የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰላም አስከባሪ ሃይል በሚል ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በዶላር ቢልክም እግረኛው ሰራዊት የሚከፈለው ገንዘብ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ፣ የክፍያ መጠኑ እስካልተሻሻለ ድረስ አንዘምትም” ብለዋል።
ወታደራዊ አዛዦች ከፍተኛ ገንዘብ ሲከፈላቸው ሌላው ወታደር ቤተሰቡን ለማኖር በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ወታደሮች በመጥቀስ ጥሪ ላቀረበላቸው አካል መልስ መስጠታቸው ታውቋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s