የብሄር ብሄረሰቦች በአል የህወሃት ባለስልጣናት የገንዘብ ምንጭ ሆነው ቀጥለዋል

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ ህዳር 29 የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል አምና በጅጅጋ ሲከበር ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ሲያስወጣ ዘንድሮ ደግሞ በአሶሳ በሚከበረው እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያስወጣል።
ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት የብሄር ብሄረሰቦችንም ሆኑ የባንዲራ፣ የመከላከያና ሌሎች አገር አቀፍ በአላትን በብቸኝነት ለማዘጋጀት የተፈቀደለት ወዛም ኮሚኒኬሽን የተባለው ድርጅት ለህወሃት ባለስልጣናት ገቢ ማስተላለፊያ ድርጅት ሆኖ በማገልገል ላይ ነው።
ድርጅቱ የበአላት ዝግጀቶችን ያለጫረታ በመውሰድ በአንድ ዝግጅት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያስተላልፋል። በዚህ አመት በሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል ላይ ወዛም ኮሚኒኬሽን በአለም ላይ በእርዝመቱ ተወዳዳሪ የሌለውና ጊነስ ቡክ ላይ የሚጸፍ ሰንደቃላማ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለማሰራት እቅድ አውጥቶ ስራውን ለመስራት ከመከላከያ ኢነጀሪንግ ባለስልጣናት ፈቃድ መጠየቁን ጠቁመዋል። የድርጅቱ መሪ ሃሳቡን ሳውድ አረቢያ በመሄድ ያገኘው ሲሆን፣ ሳውድ አረቢያ በረጅም ሰንደቅአላማዋ ጊነስ ቡክ ላይ መስፈሩዋን በመጥቀስ በቤንሻንጉል ክልል የሚሰራው ሰንደቅ አላማ ከዚህ እንዲበልጥ ሃሳብ አቅርቧል። ሰንደቅ አላማው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ የሚያስወጡ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምእራፍ ለመጨረስ 80 ሚሊዮን ብር እንዲፈቀድለት ጠይቋል። ሰንደቅ አላማው ለዚህ አመት የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እንዲደርስ መታሰቡን ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት የዚሁ ሰንደቅ አላማ ዲዛይን የደረሰው ሲሆን፣ ገንዘቡ ተፈቅዶ ስራው ተጠናቆ በዚህ አመት በሚደረገው በአል ላይ ይመረቅ አይመረቅ እስካሁን ለማወቅ አልቻለም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ እጅግ ግዙፍ የሆነ የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶግራፍ በክልሉ ለመስቀል ሃሳብ አቅርቧል። ለዚህም ስራው በ10 ሚሊዮን ብሮች የሚጠጋ ገንዘብ ጠይቋል።
የድርጅቱ ስራአስኪያጅ በተለያዩ አለማት በመዘዋወር ፎቶግራፎችን ይዘው በመምጣት የፕሮጀክት ፈቃድ ለህወሃት ባለስልጣናት በማቅርብ፣ ያለምንም ተጫራጭ እንዲወስድ ይደረጋል። ድርጅቱ ፕሮጀክቱን ከወሰደ በሁዋላ ሌሎችን ንዑስ ድርጅቶች ቀጥሮ ያሰራል። ድርጅቱ በየአመቱ ከክብረበአላት የሚያገኘውን ገቢ ለህወሃት ባለስልጣናት እንደሚያካፍል ምንጮች ገልጸዋል።
አምና በጅጅጋ በተካሄደውን ዝግጅት አጠቃላይ ዝግጅቱን የወሰዱት የህወሃት ሰዎች ሲሆን፣ በዚህም በመቶ ሚሊዮኖች ትርፍ አድርገዋል። በዚህ አመት በአሶሳ በሚደረገው በአል ላይም ከምግብና ውሃ አቅርቦት ጀምሮ ማንኛውንም አይነት ዝግጅቶች ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር የጥቅም ትስስር የፈጠሩ ድርጅቶች ያዘጋጁታል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚዘጋጁ በአላት የህወሃትን ታላቅነት እንድናስታውስ ተብሎ ከመዘጋጀታቸው በተጨማሪ ለተወሰኑ ቡድኖች ጥቅም ማጋበሻ ሆነው እንደሚዘጋጁ ምንጮች ገልጸዋል። ከጸጥታ ሰራተኞች አንስቶ እስከበአሉ ዝግጅት የአንድ አካባቢ ሰዎች ገንነው የሚወጡት ነው የሚሉት ምንጮች፣ በገንዘብ ደረጃም ቢሆን ወጪና ገቢን በተመለከተ ማንም አይነት ኦዲት እንደማረግበትና ታክስ እንደማይከፈልበት ይገልጻሉ።
የህወሃት ባለስልጣናት በሚሰበስቡት ወሰን የለሽ ገንዘብ ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሃብት ክፍፍል ልዩነት እየፈጠረ መምጣቱን ታዛቢኦች ይገልጻሉ። በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚሰሩ ዘመናዊ ህንጻዎች እና ድርጅቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከእነዚህ ባለስልጣናት ጋር የተሳሰሩና ድጋፍ የሚደረግላቸው ናቸው።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s