9ኙ ፓርቲዎች ለሁሉም የሃይማኖት ድርጅቶች ጥሪ አስተላለፉ

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ጥሪውን ያስተላለፉት ህዳር 27 እና 28 የሚካሄደውን የ24 ሰአት የተቃውሞ ሰልፍ በማስመልከት ባወጡት መግለጫ ነው
ገዥው ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በህገ መንግስቱ ካስቀመጠውና በየ መድረኩ ከሚናገረው በተቃራኒ የእምነት ተቋም መሪዎችን ካድሬዎቹ በማድረግ ህዝብን ለመያዝ እየጣረ እንደሚገኝ የሚያትተው መረጃው፣ የገዥውን ፓርቲ አካሄድ የተቃወሙ ምዕመናን በአሸባሪነት፣ በጸረ ሰላም ኃይልነት፣ በአፍራሽነት…እና በሌሎችም ስርዓቱ በመፈረጃነት በሚጠቀምባቸው ስሞች ሲከስ፣ ሲያስርና እርምጃ ሲወስድ መቆየቱን አስታውሷል።
ባለፉት 3 አመታት መብታቸው እንዲከበር በሰላማዊ መንገድ የጠየቁት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው ታሪካዊ በደል ስርዓቱ የእምነት ነፃነትን በማታለያነት ከመጠቀም ውጭ በህገ መንግስቱ ያሰፈረውን መብት እንደማያከበር፣ ከዚህም አልፎ ጸረ እምነት ስለመሆኑ ቋሚ ማሳያ ነው የሚለው ፓርቲው፣ ስርዓቱ የተጠናወተው እምነትን በመሳሪያነት የመጠቀም፣ የእምነት መሪዎችን ካድሬ የማድረግና ህዝብን የመሸበብ መጥፎ አባዜ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይም በግልጽ ሲንፀባረቅ መቆየቱን ገልጿል።
ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፉት 24 አመታት ኦርቶዶክስ ተከታዮችን ከሌሎች የእምነት ተከታይ ኢትዮጵያን ጋር ለማጋጨት ከመጣር ባለፈ ካድሬዎች በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዲወስኑ ትልቅ ስራ መስራቱን እንዲሁም በልማት ስም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እጅግ የሚከበሩ ገዳማትን እስከ ማፍረስ መድረሱንም አትቷል።
ትብብሩ ፀረ እምነት በሆነው የገዥው ፓርቲ አካሄድ እምነታቸው እየተረገጠ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእምነት ነጻነታቸውን ለማረጋገጥ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ህዳር 27/28 ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል የሚደረገውን የአዳር ሰልፉን ቅስቀሳ እንዲደግፉና በሰልፉም በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s