ምእራባዊያን ኢህአዴግን ከተቃዋሚዎች ጋር ለማቀራረብ ላይ ታች እያሉ ነው

ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ችግር እየከፋ መሄዱ ለህዝባዊ አመጽ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት ያደረባቸው ምእራባዊያን በአሜሪካ ፊት አውራሪነት በአገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ለማቀራረብ እየተሯሯጡ መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ።
እንደምንጮች ገለጻ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ አንዳንዶችን በማካተት፣ በውጭ ከሚገኙ ገዢውን መንግስት በሃይል እናንበረክካለን ከሚሉ ወገኖች ጋር ለማቀራረብ አሜሪካውያን የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን እያነጋገሩ ሲሆን፣ ኖርዌይ ውይይቱን ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰች ነው።
ኢህአዴግ በድርድሩ ላይ ለመገኘት ፈቃደኝነቱን መግለጹ የተነገረ ሲሆን፣ በተቃዋሚዎች በኩል ግን አንዳንዶች ለውይይት ለመቀመጥ ፈቃደኝነታቸውን ሲገለጹ ሌሎች ግን እያንገራገሩ ነው።
ምርጫውን ተከትሎ ህዝባዊ አመጽ ቢነሳ ኢህአዴግ ሊወድቅ ይቻላል የሚል ስጋት የገባቸው ምእራባውያን፣ ምናልባትም ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች የተወሰኑ መቀመጫዎችን በመልቀቅ ውጥረቱ እንዲበርድ ሊያደርግ ይችላል የሚል እምነት ይዘዋል።
የአውሮፓ ህብረት ከሁለት ምርጫዎች በሁዋላ የኢትዮጵያን ምርጫ እንደማይታዘብ ባስታወቀ ማግስት የተጀመረው የአሜሪካ እና የኖርዌይ ጥረት ይሳካ አይሳካ ለወደፊቱ የሚታይ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የኖረዌይና የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶችን ለማናገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s