የኦሮምያ ክልል የአድማ ብተና ዋና አዛዥ እስከ ጠባቂዎቻቸው አረፉ

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በተለይም በአምቦ፣ በአለማያና በሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች ለተፈጸሙ ግድያዎችና በሌሎች አካባቢዎች ለደረሱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑት ኮማንደር ፣ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓም ሲያሽከረክሩት የነበረው መኪና ተገልብጦ ከ3 ጠባቂዎቻቸው ጋር በሂርናና አሰበ ተፈሪ መካከል በሚገኝ አንድ ገደላማ ቦታ ላይ ገብተው ህይወታቸው ወዲያውኑ አልፎአል።
ኮማንደሩ የተሳፈሩበት ዘመናዊ ላንድ ክሩዘር ወደ ኢትዮጵያ ከገባ የአንድ ወር እድሜ ብቻ የነበረው መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ አደጋው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ይሁን አይሁን ለማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ኢህአዴግ በኦሮምያ ክልል ውስጥ አለኝ ብሎ የሚያስበው ቁልፍ የደህንነት ሰው እንደነበር የሚናገሩት ምንጮች፣ ግለሰቡ በቀጥታ ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር እየተገናኘ የደህንነት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ በክልሉ ሲቪል ባለስልጣኖች ዘንድ እንዲፈራ አድርጎታል።
ኮማንደሩ ከቁልቢ ገብርኤል በአል ጋር በተያያዘ የጸጥታውን ሁኔታ ለመቃኘት ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን ለማወቅ ተችሎአል። ኮማንደር ጌትነት በ1995 እና 96 በክልሉ ተሰማርተው ነበሩ አድማ በታኝ ፖሊሶችን ማሰልጠኑን፣ በሂደትም ባለው የፖለቲካ ታማኝነት የክልሉ አድማ በታኝ አዛዥ ሆነ ለመሾም መብቃቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s