ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። >> ነው ሲል ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለነፃነት ንቅናቄ ገለጸ።

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንቦት 7 <> በሚል ርእስ ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን ባስነበበው ርእሰ-አንቀጽ፤በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እሁድ እለት በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለ 10 ደቂቃ አቅርቦት እንደነበር በማውሳት፤ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ሁኔታ ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑና አቶ አንዳርጋቸው በትክክል ምን እንዳለ የሚያስረዳ ባለመሆኑ፤ በይዘቱ ላይ አስተያዬት መስጠት አስፈላጊ እንዳልሆነ ገልጿል።
ከዚያ ይልቅ ህወሀት አንዳርጋቸውን ለምን አሁን ሊያቀርበው ፈለገ?የሚለውን ነጠብ ማዬት እንደሚያስፈልግ የጠቆመው ግንቦት 7፤ ህወሀት በውስጥም፣በውጪም በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባበት ወቅት በመሆኑ በተለይ ውስጣዊ ውጥረቱን ለማስተንፈስና አቅጣጫ ለማስቀየር አንዳርጋቸውን በተቆተራረጠ ምስልና ድምጽ አጅቦ ማቅረቡን ጠቅሷል። <>ያለው ግንቦት 7፤ ህወሓት፣ የኢትዮጵያን መከላከያ ጦር ሠራዊት ዘረኛ በሆነ መንገድ አደራጅና ከፍተኛ አመራሩን በታማኝ አባላቱ ሞልቶ ተደላድሎ የተቀመጠ መስሎ ቢቆይም አሁን ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ህወሓትን የማገልገል ፍላጎት እንደሌላቸውና ይልቁንም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም የህወሓትን ውድቀት ለማፋጠን ያላቸውን ጉጉት በግልጽ እያሳዩ መሆናቸውን መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ አብራርቷል።
እንደ አየር ኃይል ተቃውሞ ገሀድ የወጣ ዜና አይሁን እንጂ በሌሎችም የሠራዊቱ ክንፎች ያለው አመጽ ተመሳሳይ የጡዘት ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጸው ግንቦት 7፤ብአዴን እና ኦህዴድ ውስጥም ለአገራቸው ለኢትዮጵያ እና እንወክለዋለን ለሚሉት ሕዝብ እና ለራሳቸው ክብር ያላቸው አባላት ብቅ ብቅ እያሉ ነው ብሏል። እነኚህንና ሌሎችንም በመላ ሀገሪቱ የተቀጣጠሉትን የመብት ጥያቄዎችና አመጾች የተነተነው ግንቦት 7፤ <>ያለው ንቅናቄው፤ ይህም ኢትዮጵያዊያን ፀሐይና ብርድ ሳይበግራቸው “እኔ አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” እያሉ በእንግሊዝ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች እና በአውሮፓ ኅብረት ሲያደርጓቸው የቆዩ ተቃውሞዎች ውጤታማ መሆናቸውን ነው ብሏል። <> ያለው ግንቦት 7፤ ወያኔዎች አንዳርጋቸውን ወደፊትም እንዲሁ ሊናገር ያልፈለገውን ቢያናግሩት የሚፈጠር ምንም ለውጥ እንደሌለ አስምሮበታል።
<> ያለው ግንቦት 7፤<< አንዳርጋቸውን ስናይ በህወሓት ፋሽስታዊ መዳፍ ውስጥ የወደቁብንን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖቻችንን ሁሉ ያስታውሰናል። ያነቃናል፣ ያነሳሳናል!!!”ብሏል። ንቅናቄው በመጨረሻም _<>ሲል ለ ኢት ጰያ ህዝብ ጥሪ አቅርቧል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s