ከደምሕት ጋር ግንኙነት አለህ ተብሎ የታሰረው ወጣት ሺሻይ አዘናው ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትግራይ ሕዝብ ዲሚክራሲያዊ ድርጅት ‹‹ደሚህት›› ጋር ግንኙነት ተብሎ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት የአንድነት የመቀሌ ዞን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ ወጣት ሺሻይ አዛናው በትናንትናው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት።
ወጣት ሲሳይ ቀደም ሲል በተጠየቀበት የሃያ ስምንት ቀናት ቀነ-ቀጠሮ መሰረት ትናንት በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቢቀርብም፣ ፖሊስ ማስረጃዬን ሰብስቤ አልጨረስኩም በማለት እንደገና የሃያ ስምንት ቀናት ተጨማሪ ግዜ ይሰጠው ዘንድ ጠይቋል፡፡
ጠበቃ አቶ ገበየሁ ይርዳው፣ ‹‹ፖሊስ ያቀረባቸው ምክንያቶች የህግ አግባብ እንደሌላቸው በማስረዳት፣ የደንበኛቸው ዋስትና መብት ይከበርለት ዘንድ ቢጠይቁም፤ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ተጨማሪ ግዜ ጥያቄ በመቀበል፣ ለየካቲት 4 ቀን 2007 ተለዋጪ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ወጣት ሺሻይ አዛናው፣ ከሁለት ወራት በላይ ዋስትና መብታቸው ተነፍጎና አንዳች ማስረጃ ሳይቀርብባቸው በእስር ላይ ይገኛል፡፡
<>በማለታቸው የፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው የዞን 9 ጦማርያንና ጋዜጠኞች በፍርድ ቤት ለ 15ኛ ጊዜ መቀጠራቸው ይታወቃል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s