የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር- የመንግስት ሚዲያዎችን ተቸ

ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቲቪ(ኢቢሲ) ፣ራዲዮ ፋና እና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች በምርጫው ዙሪያ ጠንካራ ስራ አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ተቸ።
የመንግስትና የድርጅት ሚዲያዎች ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ለተፎካሪ ፓርቲዎች በተሰጣቸው አጀንዳ ዙሪያ ብልጫ ያለው ስራ አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር -የኢትዩጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬትን ወቀሰ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ -ለኢቢሲ ባስተላለፈው የደብዳቤ ትእዛዝ በቀጣይ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ብዙሀን መገናኛዎች ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ በምርጫ ለኢህአዴግ ድጋፍ የሚያስገኙ ፕሮግራሞችንና ዶክመንተሪዎችን ያለማሳለስ እንዲሰሩ ከማስጠንቀቂያ ጋር እንዲነገራቸው አሳስቧል።
ሚዲያዎቹ በተለይ የደጋፊዎችን ድምጽ በማሰባሰብና የድርጅቱን ፖሊሲና ስትራቴጂ በመከተል በጽሁፎችና በፕሮግራሞች ብቃት ያላቸውን ስራዎች በተከታታይ እንዲሰሩ እንዲደረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር አስጠንቅቋል።
እስካሁን ፋና ኮርፖሬትንና ኢቢሲን ጨምሮ በክልል ያሉት ብዙሀን መገናኛዎች አማራጭ ፖሊሲዎች ላይ የአመለካከት ልዩነት እንዳለ ለማሳየት አንዳንድ ስራዎችን ቢሰሩም፤ የተሰሩት ስራዎች ጠንካራ አደሉም ተብለው ተተችተዋል፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s