በክልሎች የሚገኙ የአንድነት አመራሮች ጽ/ቤታቸውን በአቶ ትእግስቱ ለሚመራው ቡድን እንዳያስረክቡ ተጠየቁ

ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራውና በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው የአንድነት አመራር ጥር 29 ቀን 2007 ዓም የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሰባ ለማካሄድ እንዲሁም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ቀበና በሚገኘው ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ቢሮው በፖሊስ በድንገት በመከበቡ ሳይሳካ ቀርቷል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ አበበ አካሉ ለኢሳት እንደገለጹት ስብሰባውን ለማካሄድ ታስቦ የነበረው በሂደት ስለሚወሰዱት እርምጃዎች ለመነጋገር ቢሆንም በፖሊስ ህገወጥ ድርጊት የተነሳ አልተሳካም። ይሁን እንጅ በክልሎች የሚገኙ የአንድነት አመራሮችና አባላት ጽህፈት ቤቶቻቸውን የኢህአዴግ ተለጣፊ ናቸው ላሉዋቸው አቶ ትእግስቱ አወሉ ሰዎች እንዳያስረክቡ ትእዛዝ መተላለፉን ተናግረዋል።
አንድነት ከመታገዱ በፊት የፊታችን እሁድ ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥሪ አስተላልፎ ዝግጅት እያደረገ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ ቀንም በደሴ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነበር፡፡
ፓርቲው ዕውቅና መነፈጉን ተከትሎ በአንድነት ስም የሚያንቀሳቅሳቸው የሚሊዮኖች ድምጽ እና ፍኖተ ነጻነት ጋዜጦችና ድረገጾች ሕትመትና ስርጭት መቋረጡ የግድ ሆኗል፡፡ በተመሳሳይ መንገድም የመኢአድ ጽህፈት ቤት በፖሊሶች ጥበቃ ስር በመዋሉ ሰራተኞች ስራቸውን ለመስራት አለመቻላቸውን የመኢአድ ዋና ጸሃፊ ተናግረዋል
አንድነትና መኢአድ የምርጫ ቦርድን ትእዛዝ ለሚያከብሩ ሰዎች ተሰጥተዋል ተብሎ በምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ፕ/ር መርጋ በቃና መነገሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያነጋገረ ይገኛል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s