በኦሮምያ ክልል የፌደራል ፖሊሶች ሁለት የቤተሰብ አባላትን በጥይት መትተው አመለጡ

የካቲት ፬(አራት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በምእራብ ሸዋ ዞን በባኮ ወረዳ በቴቢ ከተማ ከሩሰንጎት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት አቶ ተሙሻ በርጫ እና የ13 አመት ታዳጊ ልጃቸው ፋንቱ ተሙሻ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች በጥይት ተመትተው አምቦ ሆስፒታል መግባታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ታዳጊዋ ወጣት አንገቷ አካባቢ በጥይት ስትመታ፣ አባቷ ደግሞ እግራቸውን በሁለት ጥይቶች ተመተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑም ታውቋል።
ማንነታቸው ያልታወቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ቀበሌው በመሄድ፣ አቶ ተሙሻን አሸባሪዎችን አስጠግተህ ትቀልባለህ ብለው በጥይት እንደመቱዋቸውና የአካባቢው ነዋሪዎች ሆ ብለው ሲወጡ፣ በመጡበት መኪና ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
አሸባሪ የተባሉት ሃይሎች እንማን እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ነዋሪዎች ግን ምናልባትም ለምርጫ ቅስቀሳ የመጡ የተቃዋሚ አባላትን ሊሆን ይችላል ይላሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s