የኢትዮጵያ፣ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት በአባይ ጉዳይ ድንገተኛ ስብሰባ አካሄዱ።

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ተርኪሽ ፕሬስ እንዳለው፤ የሶስቱ ሀገራት ባለስልጣናት ስብሰባቸውን ያደረጉት ባለፈው ረቡእ በአዲስ አበባ ውስጥ ነው።
የሀገራቱ ባለስልጣናት ድንገተኛ ስብሰባ ለጋዜጠኞች ዝግ እንደነበርም የአናሎዱ የዜና አገልግሎት ወኪል ዘግቧል።
በስብሰባው የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሾርኪ፣ የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር ሆሳም ሞጋሲ፣ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ሞታሳ ሙሳ እና ከሶስቱም ሀገሮች የተውጣጡ ኤክስፐርቶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያና ግብጽ በ አባይ ግድብ ዙሪያ በመካከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባት ለማጥበብ እየሞከሩ ነው ተብሏል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሶስቱም ሀገሮች ተውጣጥቶ በ 2011 የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ፤በ ኢትዮጵይና በግብጽ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ ለስምንት ወራት ስራውን አቋርጦ ከቆየ በኋላ እንደገና ባለፈው ነሀሴ ወር ስራውን መጀመሩ ይታወሳል።
ኮሚቴው ባለፈው መስከረም ባደረገው ስብሰባ ፤ ግድቡ በአካባቢ እና በሀገራቱ ላይ ስለሚፈጥረው ተጽእኖ የሚያጠና ቡድን መመደቡ ይታወቃል።
እንደ ተርኪሽ ፕሬስ ዘገባ፤ ኢትዮጵያ የምትሰራው ግድብ በሀገራቱ የውሀ ፍሰት ላይ ችግር እንደማይፈጥር በተደጋጋሚ ብትገልጽም፤ ግብጽ ግን <> የሚል ከፍተኛ ስጋት አላት።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s