በሙስሊሞች ላይ በከፍተኛ የደህንነት ሃይሎች የሚመራ የእስር ዘመቻ መከፈቱ ተነገረ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍትሕ ራዲዮ እንደዘገበው፤በአዲስ አበባ ብቻ ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን ለማሰር ታቅዷል፡፡

የሙስሊሙን ማህበረሰብ አካላት  በምክንያት ለማሰር በከፍተኛ የኢትዬጲያ መንግስት የደህንነት ሃይሎች የሚመራ ዘመቻ  መከፈቱን ፍትህ ራዲዬ ዘግቧል።

ራዲዮው ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ዘመቻው ያነጣጠረው፤ ከመጪው  ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በህዝበ-ሙስሊሙ መካከል ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥሩ ይሆናል የሚል ስጋት ባሳደሩ ሙስሊሞች ላይ ነው።

መንግስት ምርጫው ከመድረሱ አስቀድሞ በሃገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተለያዩ ምክንያቶች ሲያዳክምና ሲያግድ ከመቆየቱም በላይ የግል ፕሬስ ጋዜጠኞችን ለእስርና ለስደት መዳረጉ ይታወቃል።

በአሁኑ ወቅት ሳይታገዱ  የቀሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለኢህአዴግ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ብቻ መንጠላጠል ከቻሉ ነው የሚል ግምገማ የወሰደው ኢህአዴግ፤ በዚህም መሰረት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የመጨረሻ የማዳከም ዘመቻ መከፈት አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ  መድረሱ ተመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የአሰሳ እና ስምሪት ተግባር እየተካሄደ ሲሆን፤በተለይ በአዲስ አበባና በጅማ በርካታ ሙስሊሞችን በጅምላ  የማሰሩ ዘመቻ ተጀምሯል።

እንደ ምንጮቹ መረጃ፤በከፍተኛ የደህንነት ሀይሎች በሚመራው በዚህ ዘመቻ፤ ሃገር አቀፍ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት  በአዲስ አበባ ብቻ ቁጥራቸው ከ 800 እስከ 1000 የሚደርሱ  ሰዎችን ለማሰር እቅድ ተይዟል።

በዛሬው ዕለትም የራዲዬ ቢላል ጋዜጠኛ የነበረው ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቀ በርካታ ሙስሊሞች ከያሉበት በደህንነት ሃይሎች እየታፈኑ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ሙስሊሞቹ በተያዙበት አካባቢዎች በወደሚገኙ የፖሊሰ ጣብያዎች እየታጎሩ ሲሆን፤ የመኖሪያ ቤታቸውም በፖሊሶች እና በደህንነቶች እየተፈተሸ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቤታቸው የሚገኙ የተለያዩ ላፕቶፕ እና የግል ንብረቶቻቸውም  “ለምርመራ ያስፈልጋሉ” እየተባሉ በደህንነቶች   መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s