በኣማራ ክልል 31 እስር ቤቶች አደገኛ እስር ቤቶች ተባሉ

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጃፓን መንግስት የሚደገፈው የግልግል ዳኝነት ይፋ ባደረገው ጥናታዊ ጽሁፍ በአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች በህግ ታራሚዎች አያያዝ እና አስተዳዳር ከፍተኛ ችግሮች አሉባቸው ብሎአል። 31 እስር ቤቶች በእስረኞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትሉም ተገልጿል።
ለሰው ልጆች አደገኛ ተብለው ከተለዩት እስር ቤቶች መካከል ደብረ ታቦር፣ ጋይንት፣ አዲስ ዘመን፣ ሃይቅ፣ ደብረ-ብርሃን፣ መሃል ሜዳ አዲስ ከተማ፣ አጣየ፣ ወልድያ፣ ላሊበላ፣ ከሚሴ፣ እንጅባራ፣ ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ፍኖተሰላም፣ ሶቀጣ፣ ተንታ፣ ወገን ጤና፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ቻግኒ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ብቸኛ፣ ሞጣ፣ ደሴ፣ ዳባት፣ ደባርቅ፣ ጭልጋ፣ ኮምቦልቻ፣ ቦረናና ወረ ኢሉ ናቸው።
በእነዚህ እስር ቤቶች እስረኞች ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ከሆኑ በደህንነቶች ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል የሚለው ጥናቱ፣ የእጀባ፣ የምግብና ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንዲሁም የመጠለያና መሰል ፍትህ የማህበራዊና አስተዳዳራዊ አገልግሎቶችን በተገቢው መንገድ አያገኙም ብሎአል።
የእስረኞቹ የቀን ወጪ 9 ብር ብቻ በመሆኑ በአገሪቱ ከሚታየው የኑሮ ውድነት አንጻር ለእሰረኞቹ በቂ የሆነ ምግብ ለማቅረብ ባለመቻሉ፣ እስረኞች በረሃብ ይሰቃያሉ ሲል ጥናቱ አመልክቷል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s