ኢትዮጵያ ከ15 አመታት በሁዋላ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ 1 ሺ ዶላር እንደማይደርስ አንድ የኢኮኖሚ ትንበያ አመለከተ

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመንት ባወጣው ጥናት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2030 ወይም ከ15 አመታት በሁዋላ የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 820 ዶላር ይደርሳል። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በቅርቡ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ
ካላቸው አገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ የጥናት ውጤቱ እንደሚያሳየው በ2030 ኢትዮጵያ ፣ የመካከለኛ ገቢ ዝቅተኛ መነሻ ከሆነው 1 ሺ ዶላር ለመድረስ አትችልም ።
በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከ1 ሺ ዶላር በላይ የነፍስ ወከፍ ገቢ እንደሚያስመዘግቡ ጥናቱ ያመለክታል። እኤአ በ2030 ሲሸልሽ የነፍስ ወከፍ ገቢዋን 22 ሺ 917 ዶላር በማድረስ ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች። ኬንያ 1 ሺ 900 ዶላር፣ ዩጋንዳ 1 ሺ 93 ዶላር፣ ሱዳን 2 ሺ ዶላር፣
ግብጽ 4 ሺ 857 ዶላር ጋቦን 15 ሺ 928 ዶላር ፣ ሞሪሺየስ 14 ሺ 862 ዶላር እንዲሁም ዚምባብዌ 1 ሺ 287 ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ይኖራቸዋል። ከጎረቤት አገራት ኤርትራ 480 ዶላር እንዲሁም ጅቡቲ 434 ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ይኖራቸዋል።
በ2030 ናይጀሪያ አጠቃላይ ምርቷን ወደ 1 ትርሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በኢኮኖሚም በህዝብ ብዛትም በአፍሪካ ቀዳሚ አገር ትሆናለች።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s